ሮሜ 11:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እናንተ አሕዛብ ግን በተፈጥሮ የዱር የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች ሆናችሁ ሳለ ያለ ቦታችሁ በጓሮ የወይራ ዛፍ ላይ መተከል ከቻላችሁ እነዚህ በተፈጥሮአቸው የጓሮ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆኑት አይሁድማ ወደ ቀድሞው ቦታቸው ተመልሰው መተከል እንዴት አይቻላቸውም! 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የበረሓ ከሆነው የወይራ ዛፍ የተቈረጥህና ተፈጥሮህ ወዳልሆነው ወደ መልካሙ ወይራ የገባህ ከሆንህ፣ በተፈጥሯቸው ቅርንጫፎቹ የሆኑት እነዚህ ወደ ራሳቸው ወይራ ዛፍ መግባታቸውማ ምን ያህል ይሆን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 አንተ በተፈጥሮ የበረሃ ከነበረ የወይራ ዛፍ ተቆርጠህ እንደ አፈጣጠርህ ሳትሆን በመልካም የወይራ ዛፍ ከገባህ፥ ይልቁንስ እነዚያ በተፈጥሮአቸው ቅርንጫፎች የሆኑት በራሳቸው የወይራ ዛፍ እንዴት አይገቡም? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 አንተ የዱር ወይራ፥ አንተን ስንኳ ከበቀልህበት ቈርጦ ባልበቀልህበት በመልካሙ ዘይት ስፍራ ከተከለህ፥ ይልቁን ጥንቱን ዘይት የነበሩትን እነዚያን በበቀሉበት ስፍራ እንዴት አብልጦ ሊተክላቸው አይችልም? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበረ ወይራ ተቆርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ፥ ይልቁንስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም? 参见章节 |