Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ለእናንተም በሮም ለምትኖሩ ወንጌልን ላስተምራችሁ እመኛለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በሮም ለምትኖሩ፣ ለእናንተም ወንጌልን ለመስበክ የምጓጓው ለዚህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ እጓጓለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ይል​ቁ​ንም በሮሜ ላላ​ችሁ ለእ​ና​ንተ ወን​ጌ​ልን ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ እተ​ጋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ።

参见章节 复制




ሮሜ 1:15
12 交叉引用  

እግዚአብሔርም አባቴን ዳዊትን ‘ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ ትሠራ ዘንድ በልብህ ማሰብህ መልካም ነው።


ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ማንን እልካለሁ? መልእክተኛ የሚሆንልንስ ማን ነው?” ሲል ሰማሁት፤ እኔም “እነሆ እኔ እሄዳለሁ! እኔን ላከኝ!” አልኩ።


እንግዲህ ሠራተኞችን ወደ መከሩ ሥራ እንዲልክ የመከሩን ጌታ ለምኑት።”


ይህች ሴት የተቻላትን አድርጋለች፤ ሥጋዬም ከመቀበሩ በፊት አስቀድማ ለማዘጋጀት ሽቶ ቀባችው።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።


ጳውሎስ ግን “እንደዚህ እያለቀሳችሁ ስለምን ልቤን በሐዘን ትሰብሩታላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።


አስተማሪዎች ካልተላኩስ እንዴት ቃሉን ሊያስተምሩ ይችላሉ? ይህም “የመልካም ዜና አብሣሪዎች መምጣት እንዴት ደስ ያሰኛል!” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ።


የዘወትር ምኞቴም ሌላው ሰው በጣለው መሠረት ላይ መገንባት ሳይሆን የክርስቶስ ስም ባልተሰማበት ስፍራ ሁሉ መልካሙን ዜና ማብሠር ነው።


የወንጌልን ቃል ያለ ግዴታ በፈቃዴ ባበሥር የድካም ዋጋ ይኖረኛል፤ በግዴታ ባደርገው ግን በዐደራ የተሰጠኝን ኀላፊነት ፈጸምኩ እንጂ ሌላ ያደረግኹት ነገር አለ ማለት አይደለም።


ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም።


跟着我们:

广告


广告