Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም “እነሆ! እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ!” አለ፤ ቀጥሎም “ይህ ቃል የታመነና እውነት ስለ ሆነ ጻፍ” አለኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም፣ “እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” አለ፤ ደግሞም፣ “ይህ ቃል የታመነና እውነት ስለ ሆነ ጻፍ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። እኔንም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። ለእኔም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።

参见章节 复制




ራእይ 21:5
14 交叉引用  

እነሆ፥ እኔ አስቀድሜ የተናገርኳቸው ነገሮች ሁሉ ተፈጽመዋል፤ አሁን ደግሞ ወደ ፊት ስለሚሆኑት አዳዲስ ነገሮች፥ ከመፈጸማቸው በፊት እናገራለሁ።”


ይልቅስ የማደርገውን አዲስ ነገር ተመልከቱ፤ እርሱም በመፈጸም ላይ ስለ ሆነ ልታዩት ትችላላችሁ፤ በበረሓ መንገድን አወጣለሁ፤ በምድረ በዳም ወንዞችን አፈልቃለሁ።


ስለዚህ አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል፤


ስለዚህ ማንም ሰው የክርስቶስ ወገን ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ፍጥረት አልፎአል፤ በእርሱም ስፍራ አዲስ ፍጥረት ተተክቶአል።


ይህ “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡ ነገሮች ጸንተው እንዲኖሩ የሚናወጡ ወይም የተፈጠሩ ነገሮች መወገዳቸውን ነው።


“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”


እንግዲህ ያየኸውን፥ አሁን ያለውንና በኋላ የሚመጣውን ጻፍ።


ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ በጉ ሠርግ ግብዣ የተጠሩ የተባረኩ ናቸው” ብለህ ጻፍ አለኝ፤ ቀጥሎም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው” አለ።


ከዚህ በኋላ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በዙፋኑም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም፤


ማንም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ነገር ቢያጐድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተነገሩት ከሕይወት ዛፍ ፍሬና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ድርሻውን ያጐድልበታል።


ከዚህ በኋላ መልአኩ እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃላት የታመኑና እውነተኞች ናቸው፤ ነቢያትን የሚያናግር አምላክ በቅርብ ጊዜ የሚሆነውን ነገር ለአገልጋዮቹ ለመግለጥ መልአኩን ላከ።”


ወዲያውኑ በመንፈስ ተመሰጥሁ፤ እነሆ በሰማይ ዙፋን አየሁ፤ በዙፋኑም ላይ አንድ አካል ተቀምጦበት ነበር።


እንስሶቹ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለሚኖረው ገናናነት፥ ክብርና ምስጋና በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ፥


በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ፥ በውስጥና በውጪ የተጻፈበት በሰባት ማኅተም የታሸገ የብራና ጥቅል መጽሐፍ አየሁ፤


跟着我们:

广告


广告