Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 21:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዐሥራ ሁለት ደጃፎች ያሉት ታላቅና ረጅም የግንብ አጥር ነበራት፤ በዐሥራ ሁለቱም ደጃፎች ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆመው ይጠብቁ ነበር፤ በደጃፎቹም ላይ የዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዐሥራ ሁለት በሮች የነበሩት ትልቅና ረዥም ቅጥርም ነበራት፤ በበሮቹም ላይ ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆመውና የዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ስም ተጽፎ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆመው ነበር፤ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፥ አሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ፥ የአሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።

参见章节 复制




ራእይ 21:12
21 交叉引用  

እኛ ባርያዎች ነበርን፤ አንተ ግን ባርያዎች ሆነን እንድንቀር አልተውከንም፤ አንተ የፋርስ ነገሥታት እንዲራሩልንና በሕይወት ነጻ ወጥተን ቀደም ሲል ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስህን እንደገና መልሰን እንድንሠራ፥ እዚህም በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሰላም እንድንኖር ፈቀድክልን።


የኢየሩሳሌም ከተማ ቅጽር የምረቃ በዓል በተከበረበት ዕለት ሌዋውያኑ በጸናጽል፥ በበገናና በመሰንቆ በዓሉን እንዲያከብሩ ከየሚኖሩበት ስፍራ ተፈልገው መጡ።


በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤ በቤተ መንግሥትሽም ውስጥ ጸጥታ ይኑር።”


አምላክ ሆይ! ጽዮንን ለመርዳት፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመገንባት እባክህ ፈቃድህ ይሁን።


ለእስራኤል ነገዶች መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ ከእነዚህ ዐሥራ ሁለት የዕንቊ ድንጋዮች በእያንዳንዱ ላይ ከያዕቆብ ልጆች የአንዱ ስም ይቀረጽበታል።


የግንቦችሽን ጒልላት በቀይ መረግድ፥ የቅጽር በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቊ፥ በዙሪያሽ ያለውንም ቅጽር በከበሩ ድንጋዮች አንጻለሁ።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።


በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው ዘወትር በሰማይ ያለውን ያባቴን ፊት ስለሚያዩ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ። [


ንስሓ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ በእግዚአብሔር መላእክት ዘንድ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”


“ከዚህም በኋላ ድኻው ሰው ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት፤ እንዲሁም ሀብታሙ ሰው ሞተና ተቀበረ።


ወደዚህ ተስፋ ለመድረስ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን እግዚአብሔርን ሌት ተቀን እያመለኩ ይጠባበቁ ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! እኔም በአይሁድ የተከሰስኩበት በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው።


ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ የሚድኑትን ሰዎች ለማገልገል የሚላኩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት አይደሉምን?


በምሥራቅ ሦስት ደጃፎች በሰሜን ሦስት ደጃፎች፥ በደቡብ ሦስት ደጃፎች፥ በምዕራብ ሦስት ደጃፎች ነበሩ።


የተናገረኝም መልአክ ከተማይቱንና ደጃፎችዋን፥ የግንቡንም አጥር የሚለካበት የወርቅ ዘንግ ነበረው፤


በዚያች ከተማ ሌሊት ስለሌለ ደጃፎችዋ በማንኛውም ቀን አይዘጉም።


ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告