Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 16:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ይህን የመሰለ ታላቅ የምድር መናወጥ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ ሆኖ አያውቅም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም መብረቅ፣ ድምፅ፣ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ የምድር መናወጥ ታይቶ አይታወቅም፤ ነውጡም እጅግ ታላቅ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ነውጡ እጅግ ትልቅ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ።

参见章节 复制




ራእይ 16:18
8 交叉引用  

የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።


ያ ራእዩን ያብራራልኝ የነበረው መልአክ እንደገና እንዲህ አለኝ፦ “ሕዝብህን የሚጠብቀው ታላቁ አለቃ ሚካኤል በዚያን ጊዜ ይገለጣል፤ የሰው ዘር ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ ነገር ግን ስማቸው በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈ የአገርህ ሕዝቦች ብቻ በዚያን ጊዜ ይድናሉ፤


በዚያን ጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ፥ ወደፊትም እርሱን የሚመስል ከቶ የማይሆን፥ ታላቅ መከራ ይሆናል።


በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።


በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።


ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጡ ነበር፤ በዙፋኑ ፊት የሚበሩ ሰባት ችቦዎች ነበሩ፤ እነርሱ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።


ከዚህ በኋላ በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከትኩ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ጥቊር የሐዘን ልብስ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤


ከዚህ በኋላ መልአኩ ጥናውን ይዞ ከመሠዊያው እሳት ሞላበትና ወደ ምድር ወረወረው፤ ነጐድጓድ፥ ድምፅ፥ መብረቅ፥ የምድር መናወጥም ሆነ።


跟着我们:

广告


广告