Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 98:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በገና በመደርደርና በመዘመር ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤ በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለጌታ በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ፈጣ​ሪ​ያ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ ከእ​ግሩ መረ​ገጫ በታ​ችም ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል።

参见章节 复制




መዝሙር 98:5
11 交叉引用  

ዳዊት “በገና፥ መሰንቆና ጸናጽል በመሳሰሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ የደስታ መዝሙሮችን ይዘምሩ ዘንድ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ሌዋውያንን ሹሙአቸው” በማለት የሌዋውያኑን መሪዎች ተናገረ፤


በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔር በነቢዩ ጋድና በነቢዩ ናታን አማካይነት ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውንና ዳዊትም ተግባራዊ ያደረገውን ትእዛዝ በመከተል በበገና፥ በጸናጽልና በመሰንቆ የሠለጠኑ ሌዋውያንን በቤተ መቅደሱ ውስጥ መደበ፤


ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ በገና እየደረደራችሁ ለአምላካችን ዘምሩ።


እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።


አምላኬ፥ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ! ስለ ታማኝነትህ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ በመሰንቆም የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።


“እኔ እግዚአብሔር ጽዮንንና ባድማ የሆኑባትን ቦታዎችዋን ሁሉ አጽናናለሁ፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔደን፥ በረሓዋንም እንደ ገነት አደርጋለሁ፤ በእርስዋም ተድላና ደስታ ይገኛል፤ እንዲሁም የምስጋና መዝሙር ድምፅ ይሰማል።


የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸው በገና ይዘው ነበር፤ እንዲሁም የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር።


跟着我们:

广告


广告