15 ፍትሕ እንደገና የዳኝነት መሠረት ትሆናለች፤ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይደግፉአታል።
15 ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል፤ ልባቸውም ቀና የሆነ ሁሉ ይከተሉታል።
15 ፍርድ ወደ ጽድቅ እስክትመለስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
ይሁን እንጂ ጻድቃን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ አይሉም፤ ንጹሖችም በብርታት ላይ ብርታትን ይጨምራሉ።
“ምንም እንኳ እግዚአብሔርን አላየውም ብትል ጉዳይህ በእርሱ ፊት ስለ ሆነ በትዕግሥት ልትጠብቀው ይገባል።
ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፤ ትእዛዙንም ፈጽም፤ እርሱም ምድርን በማውረስ ያከብርሃል፤ ክፉዎች ሲወገዱም ታያለህ።
በዚያን ጊዜ ሰዎች “ጻድቃን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ አገኙ፤ በዓለም ላይ የሚፈርድ አምላክ በእርግጥ አለ” ይላሉ።
እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።
ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
የተቀጠቀጠ ሸምበቆን እንኳ አይሰብርም፤ ሊጠፋ የተቃረበውንም መብራት አያጠፋም፤ በታማኝነት ፍትሕን ያስገኛል።
እግዚአብሔርን በድዬዋለሁ፤ ስለዚህም እርሱ የቀረበብኝን ክስ ተመልክቶ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቊጣውን እታገሣለሁ፤ በመጨረሻም እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ ፍትሕንም ይሰጠኛል።
በዚያን ጊዜ በጻድቅና በኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር በሚታዘዝና በማይታዘዝ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት እንደገና ታያላችሁ።”
እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።