Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አሕዛብን ገሠጽክ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ትክክለኛ ፍርድና ዳኝነት አድርገህልኛልና፥ በጽድቅ እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አሕ​ዛ​ብን ገሠ​ጽህ፥ ዝን​ጉ​ዎ​ችም ጠፉ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደመ​ሰ​ስህ።

参见章节 复制




መዝሙር 9:5
24 交叉引用  

አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።


እንደዚህ ቢያደርጉ መንግሥታትን ለማሸነፍ፥ አሕዛብንም ለመቅጣት፥


አሕዛብ ስለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?


ሐሰት የሚናገሩትን ሁሉ ታጠፋለህ፤ ነፍሰ ገዳዮችንና አታላዮችን ትጸየፋለህ።


ክፉዎች ከክፋታቸው የማይመለሱ ከሆነም፥ እግዚአብሔር ሰይፉን ይስላል፤ ቀስቱንም ያመቻቻል።


ከእነርሱ በፊት አሕዛብን አባረረ፤ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገዶች አከፋፈለ፤ ቤቶቻቸውንም ለራሱ ሕዝብ ሰጠ።


ለምን አሕዛብ “አምላካቸው የት አለ?” ብለው ይጠይቁ? የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም እንደምትበቀል በፊታችን ለአሕዛብ አሳውቅ።


የጻድቅ ሰው መታሰቢያ ለበረከት ይሆናል የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።


የጻድቃን ብርሃን ያንጸባርቃል፤ የኃጢአተኞች መብራት ግን ይጠፋል።


ንጉሣቸውንና መሪዎቻቸውን አጠፋለሁ፤ ዙፋኔንም በዚያ እዘረጋለሁ።


“ጌታ ሆይ! የእኔን ጉዳይ ተከታትለህ ሕይወቴን አዳንክ።


እኔ ይህን በማደርግበት ቀን ክፉዎች በእግራችሁ ጫማ ሥር እንደ ዐመድ ሆነው ይረገጣሉ።


እንግዲህ ተወኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ሊያስታውሳቸው በማይችል ሁኔታ ልደምስሳቸው፤ ከዚያም በኋላ አንተን ከእነርሱ ይበልጥ ኀይልና ብዛት ላለው ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።’


ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤


ዳዊትም እንዲህ አላት፤ “ከእኔ ጋር እንድትገናኚ አንቺን ወደ እኔ የላከ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን!


ዳዊትም የናባልን መሞት በሰማ ጊዜ “እኔን በመስደቡ እግዚአብሔር ናባልን ስለ ተበቀለውና እኔንም ከስሕተት ስለ ጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ ናባልን ስለ ክፉ ሥራው ቀጥቶታል” አለ። ከዚህም በኋላ ዳዊት ወደ አቢጌል መልእክተኛ ልኮ ሊያገባት መፈለጉን ገለጠላት።


ጋሻጃግሬው የነበረውንም ወጣት “እነዚህ ያልተገረዙ እኔን ወግተው በመሳለቅ መጫወቻ እንዳያደርጉኝ አንተ ራስህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ፈርቶ አልገደለውም፤ ስለዚህም ሳኦል ራሱ የገዛ ሰይፉን ወስዶ በስለቱ ላይ ወደቀበት።


跟着我们:

广告


广告