25 ግዛቱንም በባሕርና በወንዞች ማዶ በሚገኘው ምድር ላይ አደርግለታለሁ።
25 እጁን በባሕር ላይ፣ ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።
25 እውነቴና ጽኑ ፍቅሬም ከእርሱ ጋር ነው፥ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።
የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።
ከዳዊት ዘር ንጉሥ እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ የቀባሁትንም ኀያል አደርገዋለሁ።
ለምነኝ፤ አሕዛብ ሁሉ እንዲገዙልህ አደርጋለሁ፤ ምድርም በሙሉ የአንተ ርስት ትሆናለች።
ቅርንጫፎችዋን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ዘረጋች።
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።
እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።”