Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 86:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ጌታ አምላኬ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘለዓለም አከብራለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለዘለዓለምም ስምህን አከብራለሁ፥

参见章节 复制




መዝሙር 86:12
19 交叉引用  

አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ክቡር ስምህንም እናወድሳለን።


ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።


በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።


ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር በአንደበቴ ነው።


አምላክ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ያደረግኸውንም ድንቅ ነገር ሁሉ እናገራለሁ!


በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ለስምህ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።


በዚያን ዘመን እንዲህ ብለህ ትዘምራለህ፦ “ጌታ ሆይ! ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ቊጣህን መልሰህ ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።


ሲሄዱም ውሃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ፥ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለ። [


እንዲሁም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር በአንድ ልብና በአንድ ቃል እንድታከብሩት ያድርጋችሁ።


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።


እርሱ በዋጋ ገዝቶአችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።


በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊም ዜማ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በውዳሴና በመዝሙር በሙሉ ልባችሁ ጌታን አመስግኑ፤


እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኀይልህ ውደድ፤


跟着我们:

广告


广告