61 የኀይሉና የክብሩ መታወቂያ ምልክት የነበረችውን የቃል ኪዳን ታቦት፥ ጠላቶች ማርከው እንዲወስዱአት አደረገ።
61 የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።
61 ኃይላቸውን ለምርኮ፥ ሽልማቱንም በጠላት እጅ ሰጠ።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አሁን ተነሥተህ ከኀያሉ ታቦትህ ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ና፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በበረከትህ ይደሰቱ፤
እግዚአብሔር ሆይ! የኀይልህ መግለጫ ከሆነችው ከቃል ኪዳን ታቦት ጋር ወደምታርፍበት ወደ ቤተ መቅደስ ግባ።
እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤ ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ።
ከዚህ በኋላ ድንኳኑ በደመና ተሸፈነ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ድንኳኑን ሞላው።
የዳን ሰዎችም ያመልኩት ዘንድ ያን ጣዖት በዚያ አኖሩ፤ ከሙሴ ልጅ ከጌርሾም የተወለደው ዮናታንም ለዳን ነገድ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ። የእርሱም ዘሮች ሕዝቡ ተማርከው እስከ ተሰደዱበት ጊዜ ድረስ ማገልገላቸውን ቀጠሉ።
ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።
እርስዋም በእግዚአብሔር ታቦት መማረክ፥ በዐማትዋና በባልዋ መሞት ምክንያት ክብር ከእስራኤል ተለየ ስትል ልጅዋን ኢካቦድ ብላ ሰየመችው።
የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፍልስጥኤም ሰባት ወር ከቈየ በኋላ፥