54 ወደ ተቀደሰችው ምድሩ፥ በኀይሉ ወደያዛት ወደ ተራራማዋ አገር አመጣቸው።
54 ቀኝ እጁም ወዳስገኘችው ወደዚህ ተራራ፣ ወደ ቅድስት ምድር አገባቸው።
54 ወደ መቅደሱም ተራራ አገባቸው፥ ቀኙ ወደ ገዛችው ወደዚህች ተራራ፥
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
እናንተ ባለ ብዙ ወጣ ገብ ተራራዎች፥ እግዚአብሔር ሊኖርበት ወደ መረጠው ተራራ በቅናት የምትመለከቱት ለምንድን ነው? በዚያ እኮ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖርበታል።
በማይለወጥ ፍቅርህ ያዳንካቸውን ሕዝብ መራህ፤ በብርታትህም ወደ ተቀደሰችው ምድር እንዲገቡ አደረግህ፤
አምላክ ሆይ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ፥ ወገኖችህን አንተ ታስገባቸዋለህ፤ በርስትህ ተራራም ትተክላቸዋለህ።
በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ምንም ጒዳት አይደርስም፤ ባሕር በውሃ እንደሚሞላ ምድርም እግዚአብሔርን በሚያውቁና በሚያከብሩ ሰዎች ትሞላለች።
ነገር ግን ወደዚህች ምድር መጥተው ከወረሱአት በኋላ ለቃልህ መታዘዝንና በአስተማርካቸው ሕግ ጸንተው መኖርን እምቢ አሉ፤ ያዘዝካቸውንም ነገር ሁሉ አልፈጸሙም፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ሁሉ ጥፋት አመጣህባቸው።
በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”
ይህ መንፈስ ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን በሙሉ እስኪዋጅ ድረስ ልናገኝ ላለው ርስታችን መያዣችን ነው።