42 እነርሱን ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን ቀንና ታላቅ ኀይሉን አላስታወሱም።
42 እነርሱን በዚያ ቀን ከጠላት የታደገበትን፣ ያን ኀይሉን አላስታወሱም፤
42 እነርሱም እጁን አላሰቡም፥ ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን ቀን፥
በግብጽ ሳሉ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ።
ያሳያቸውን ተአምራት ሁሉ እና ያደረገውን መልካም ነገር ሁሉ ረሱ።
ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።
ይህ ሁሉ እንደሚሆን ገና ከዚያ ሳንወጣ ነግረንህ አልነበረምን? እንዲያውም ‘እባክህ ተወን፥ ለግብጻውያን ባርያዎች ሆነን እናገልግል’ ብለንህ ነበር፤ በእርግጥም በዚህ በረሓ ከመሞት፥ በዚያ ባርያዎች ሆነን መኖር በተሻለን ነበር።”
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
በተአምራትና በአስደናቂ ሁኔታ፥ በኀይልህና በታላቅነትህ፥ እንዲሁም በአስፈሪ ግርማህ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አወጣህ፥
የእስራኤልም ልጆች በዙሪያቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው ሁሉ ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ።