Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 78:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱ ግን እግዚአብሔርን በመበደል ኃጢአት መሥራት ቀጠሉ፤ በበረሓም በልዑል እግዚአብሔር ላይ ዐመፁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱ ግን በምድረ በዳ በልዑል ላይ በማመፅ፣ በርሱ ላይ ኀጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን ይበድሉት ዘንድ እንደገና ደገሙ፥ ልዑልንም በምድረ በዳ አስቈጡት።

参见章节 复制




መዝሙር 78:17
9 交叉引用  

ይህም ሁሉ ሆኖ ሕዝቡ ኃጢአት ከመሥራት ገና አልተገታም፤ ብዙ ተአምራት ቢያሳያቸውም በእርሱ አላመኑም።


ሆኖም እነርሱ የእርሱን ቅዱስ መንፈስ አሳዘኑ፤ ስለዚህ እሱ በእነርሱ ላይ ተነሥቶ ቀጣቸው።


ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።


የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤


በሲና በረሓ እንኳ እናንተን ለማጥፋት እስኪነሣሣ ድረስ እግዚአብሔርን በብርቱ አስቈጥታችሁታል።


跟着我们:

广告


广告