Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 74:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ጭቈና የደረሰባቸው ሰዎች ዐፍረው ወደ ኋላ እንዲመለሱ አታድርግ፤ ድኾችና ምስኪኖች ስምህን እንዲያመሰግኑ ይሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የተጨቈኑት ዐፍረው አይመለሱ፤ ድኾችና ችግረኞች ስምህን ያመስግኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፥ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።

参见章节 复制




መዝሙር 74:21
9 交叉引用  

“እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” የሚለውን መዝሙር በመቀባበል ለእግዚአብሔር ክብር ዘመሩት፤ የቤተ መቅደሱ መሠረት የማኖር ተግባር ስለ ተጀመረም እያንዳንዱ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እልል በማለት እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር።


እግዚአብሔር በሚሠራው ሁሉ ጻድቅ ነው፤ ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል።


እኔ ድኻና ምስኪን ነኝ፤ የደረሰብኝም መከራ ልቤን አቊስሎታል።


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤ ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥ ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ እንደ አንተ ያለ ማነው?


ችግረኞች ዘወትር እንደ ተረሱ አይቀሩም፤ የድኾችም ተስፋ ከንቱ ሆኖ ለዘለዓለም አይጠፋም።


እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


跟着我们:

广告


广告