Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 7:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ካላዳንከኝ ግን እንደ አንበሳ ነጥቀው ማንም ሊታደገኝ ወደማይችል ስፍራ ይወስዱኛል፤ ሰባብረውም ያደቁኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ነፍ​ሴን እንደ አን​በሳ እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት፥ የሚ​ያ​ድ​ንና የሚ​ታ​ደግ ሳይ​ኖር።

参见章节 复制




መዝሙር 7:2
18 交叉引用  

ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤


በደለኛ አለመሆኔንና ከአንተም እጅ ማንም ሊያድነኝ እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።


እርሱም እንደ አንበሳ ተደብቆ ይቈያል፤ ድኾችን ለመያዝ ይሸምቃል፤ እነርሱንም በአሽክላው ይዞ ይጐትታቸዋል።


እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤ እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ።


አምላክ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለ ሆነ ጠብቀኝ፤


እነርሱ እንደ ተራቡ አንበሶች ወይም እንደ ሸመቁ ደቦል አንበሶች ናቸው።


የሚበላውን ነገር አድኖ ለመቦጫጨቅ እንደሚያገሣ አንበሳ ጠላቶቼ አፋቸውን ከፈቱብኝ።


ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።


በተደናቀፍኩ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰባሰቡ፤ የማላውቃቸው ጋጠወጦች መጥተው ያለማቋረጥ አላገጡብኝ።


“ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።


ከነዚያ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከነዚያም ነፍሰ ገዳዮች ታደገኝ።


የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው።


እስከ ንጋት ድረስ ስጮኽ ዐድራለሁ፤ እንደ አንበሳም አጥንቶቼን ሁሉ ሰባበርክ፤ ሌሊትና ቀንም ለሥቃይ አሳልፈህ ሰጠኸኝ።


ስለ ጋድ ነገድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት ያሰፋ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ጋድ ክንድን ወይም ግንባርን ለመስበር፥ እንደ አንበሳ ያደባል።


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይንጐራደዳል።


የላይሽ ሕዝብ ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸውና ከሲዶንም ርቀው ይኖሩ ስለ ነበረ የሚያድናቸው አልተገኘም። ከተማዋ በቤትረሖብ አጠገብ በሚገኝ ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ የዳን ሰዎችም ከተማዋን እንደገና ሠርተው ኖሩባት።


跟着我们:

广告


广告