Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 69:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ምን ያኽል እንደምሰደብ አንተ ታውቃለህ፤ ምን ያኽል እንደ ተዋረድኩና ክብሬም እንደ ተቀነሰ ታስተውላለህ፤ እነሆ፥ ጠላቶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የደረሰብኝን ስድብ፣ ዕፍረትና ውርደት ታውቃለህ፤ ጠላቶቼንም አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ወደ ነፍሴ ቀርበህ ተቤዣት፥ ስለ ጠላቶቼም አድነኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 69:19
9 交叉引用  

ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤ የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።


ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ።


እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ ነገር ግን አባቴን አከብራለሁ፤ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ።


የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራን ሲቀበል በጽድቅ ለሚፈርደው አምላክ ራሱን ዐደራ ሰጠ እንጂ አልዛተም።


跟着我们:

广告


广告