8 አሕዛብ ሁሉ አምላካችንን አክብሩ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ለእርሱ ምስጋና አቅርቡ።
8 ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
8 አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን ባርኩ፥ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ! ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
ስሙን በማክበር ዘምሩ፤ በምስጋናም አክብሩት።
በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ! በመዝሙርና በእልልታ አመስግኑት!
በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤ የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።”
ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው!