Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 65:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስላደረግሃቸው ተአምራት ዓለም በሙሉ በፍርሃት ይዋጣል፤ በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ የእልልታ ድምፅ ይሰማል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤ የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የባሕሩን ማጓራት፥ የሞገድንም ጩኸት፥ የአሕዛብንም ማጉረምረም ዝም ታሰኛለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሕ​ዛብ ሆይ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንን አመ​ስ​ግኑ፥ የም​ስ​ጋ​ና​ው​ንም ቃል አድ​ምጡ።

参见章节 复制




መዝሙር 65:8
22 交叉引用  

ምድር እስካለች ድረስ፥ ለመዝራትና ለማጨድ፥ ለብርድና ለሙቀት፥ ለበጋና ለክረምት፥ ለቀንና ለሌሊት የማያቋርጥ ጊዜ ይኖራል።”


ኢዮብ ሆይ! በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከቶ ንጋትን አዘህ ታውቃለህን? ለንጋት ወገግታስ ቦታ መድበህለታልን?


ዐውሎ ነፋሱንና ማዕበሉን ጸጥ አደረገ።


አፋችን በሳቅ ተሞላ፤ አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤ በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን።


በዚያ ንጉሡን ፈርዖንንና አገልጋዮቹን ሁሉ ለመቅጣት ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን አደረገ።


ፀሐይ በቀን እንዲያበራ አደረገ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት። የምትበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፤


ሙሽራ ከጫጒላ ቤት እንደሚወጣ ፀሐይ ብሩህ ሆኖ ይወጣል፤ ሯጭ በሩጫ ውድድር እንደሚደሰትም ደስ ይለዋል።


ለምነኝ፤ አሕዛብ ሁሉ እንዲገዙልህ አደርጋለሁ፤ ምድርም በሙሉ የአንተ ርስት ትሆናለች።


መስኮች የብዙ በጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ ሸለቆዎች በሰብል ይሸፈናሉ፤ ሁሉም ደስ ብሎአቸው፥ በእልልታ ይዘምራሉ።


እንዲህም በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ኀይልህ እጅግ ታላቅ በመሆኑ ጠላቶችህ በፍርሃት በፊትህ ይሸማቀቃሉ።


ቀኑንና ሌሊቱን የፈጠርክ፥ ፀሐይንና ጨረቃን በየቦታቸው ያጸናህ አንተ ነህ፤


ረዓብ የተባለውን አውሬ ቀጥቅጠህ ገደልከው፤ በታላቁ ኀይልህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።


ሕዝቦች እንደ ኀይለኛ ውሃ ድምፅ ያሰማሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲገሥጻቸው በተራራ ላይ ገለባዎች በነፋስ እንደሚበተኑና በዐውሎ ነፋስም ዐቧራ እንደሚበተን ርቀው ይሸሻሉ።


በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።


በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።


跟着我们:

广告


广告