Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 61:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አምላክ ሆይ፥ ጩኸቴን ስማ፥ ጸሎቴንም አድምጥ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እርሱ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነው ሁል​ጊ​ዜም አል​ታ​ወ​ክም።

参见章节 复制




መዝሙር 61:2
20 交叉引用  

ተስፋ ለመቊረጥ ጥቂት በቀረኝ ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ያውቃል፤ ጠላቶቼ በምሄድበት መንገድ ላይ ወጥመድ ዘረጉብኝ።


ከዚህም የተነሣ መንፈሴ በውስጤ ዛለብኝ፤ ልቤም ተስፋ ቈረጠ።


እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።


እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።


በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።


ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።


አምላኬ ሆይ! ተስፋ ቈርጬአለሁ ስለዚህም ከዮርዳኖስና ከሔርሞን ምድር ከሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ? ለምንስ እጨነቃለሁ? በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


ፍርሀትና ድንጋጤ ይዞኛል፤ መላ ሰውነቴም ተሸብሮአል።


ያለ እርሱ የሚጠብቀኝና የሚያድነኝ የለም፤ መከላከያዬም እርሱ ስለ ሆነ ከቶ አልናወጥም።


የሚያድነኝ ኀያል አምባዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እርሱም እምነት የምጥልበት ምሽጌ ስለ ሆነ አልናወጥም።


ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እተክዛለሁ፤ በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ይዝላል።


ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ የተሠቃየሽ፥ በዐውሎ ነፋስም የተዋከብሽና ያልተጽናናሽ የኢየሩሳሌም ከተማ! እኔ በከበረ ድንጋይ እሠራሻለሁ፤ መሠረትሽንም የምጥለው በሰንፔር ድንጋይ ነው።


ልቡም በጣም ተጨንቆ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ሆኖ ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።


በዚያም ስትኖሩ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትናፍቃላችሁ፤ እርሱንም በሙሉ ልባችሁ ብትሹት ታገኙታላችሁ፤


跟着我们:

广告


广告