Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 60:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እናሸንፋለን፤ እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።

参见章节 复制




መዝሙር 60:12
15 交叉引用  

እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”


እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተማዎች ስንል በርትተን እንዋጋ፤ ለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን።”


የእግዚአብሔር ኀይል ከፍ ከፍ አለ፤ ኀይሉም ድል አድራጊ ነው።


መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል።


ከጠላቶቻችን ፊት እንድንሸሽ አደረግኸን፤ ጠላቶቻችንም ያለንን ሀብት ሁሉ ዘረፉን።


በአንተ ርዳታ ጠላቶቻችንን ድል እንነሣለን፤ በስምህም ተቃዋሚዎቻችንን እንረግጣለን።


ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ይመልሳል “እኔ ብቻዬን አሕዛብን ሁሉ እንደ ወይን ረገጥኩ፤ ይህን በማደርግበት ጊዜ ከሕዝቦች ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም፤ እኔ በቊጣዬ ረገጥኳቸው፤ በመዓቴም አደቀቅኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጨ።


የይሁዳ ሕዝብ ጠላቶቻቸውን ረግጠው ከመንገድ ጭቃ ጋር እንደሚለውሱ እንደ ብርቱ ጦረኞች ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ በርትተው በመዋጋት ፈረሰኞችን ሳይቀር ድል ይነሣሉ።


እኔ ይህን በማደርግበት ቀን ክፉዎች በእግራችሁ ጫማ ሥር እንደ ዐመድ ሆነው ይረገጣሉ።


በምትሄድበት ሁሉ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለምሆን አይዞህ! በርታ! አትፍራ! ብዬ አዝሃለሁ።”


አሁን እንግዲህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን በሰጠኝ ተስፋ መሠረት ይህን ኮረብታማ አገር ስጠኝ፤ ዐናቃውያን ከታላላቅ የተመሸጉ ከተሞች ጋር እንደ ነበሩ በዚያን ቀን ሰምተሃል፤ እግዚአብሔር እንዳለ እርሱ ከእኔ ጋር ሆኖ አሳድዳቸዋለሁ።


ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤


跟着我们:

广告


广告