Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 58:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤ እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ አልሰማ ብላ ጆሮዋን እንደ ደፈነች እፉኝት ናቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ያለ በደል ሮጥሁ ተዘ​ጋ​ጀ​ሁም፤ ተነሥ፥ ተቀ​በ​ለኝ፥ እይም።

参见章节 复制




መዝሙር 58:4
14 交叉引用  

ሴቲቱም “በአትክልት ቦታ ካሉት ዛፎች ፍሬ ልንበላ እንችላለን፤


የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።


በሆዱ ውስጥ ግን ወደ መራራነት ይለወጣል፤ እንደ እባብ መርዝም ይሆንበታል።


ክፉ ሰው የሚበላው ሁሉ መርዝ ይሆንበታል፤ መርዝም ሆኖ ይገድለዋል።


ምላሳቸው እንደ መርዛም እባብ ተናዳፊ ነው፤ ቃላቸውም እንደ እፉኝት መርዝ ነው።


በሂሶጵ ቅጠል ረጭተህ ኃጢአቴን አስወግድልኝ፤ እኔም እነጻለሁ። እጠበኝ፤ እኔም ከበረዶ ይበልጥ ነጭ እሆናለሁ።


እባብ ከነከሰህ በኋላ የእባብ ማፍዘዣ ድግምት ምንም አይጠቅምህም።


ጡት የሚጠባው ሕፃን በእባብ ጒድጓድ አጠገብ ይጫወታል፤ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኚት ቤት ላይ እጁን ያኖራል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተጠንቀቁ! እነሆ የአስማተኛ ድግምት ሊገታቸው የማይችል መርዘኛ እባቦችንና እፉኝቶችን በመካከላችሁ እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።”


እናንተ እባቦች፥ እባብ ልጆች፥ እንዴት ከገሃነም ቅጣት ማምለጥ ትችላላችሁ?


ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?


ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤


ወይናቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ እንደ ክፉ እፉኝትም መርዝ ነው።


ነገር ግን ምላስን ሊገራ የሚችል ማንም የለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላባትና ዕረፍት የሌላት ክፉ ነገር ናት።


跟着我们:

广告


广告