መዝሙር 50:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥ በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ከፀሓይ መውጫ እስከ ፀሓይ መግቢያ ድረስ ምድርን ጠራት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የአሳፍ መዝሙር። የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት ኀጢአቴን ደምስስ። 参见章节 |
ከመዘምራን ጐሣ የነሐስ ጸናጽል የሚያንሿሹ የኢዮኤል ልጅ ሄማን፥ የእርሱ ዘመድ የሆነው የበራክያ ልጅ አሳፍ፥ እንዲሁም ከመራሪ ጐሣ የቁሳያ ልጅ ኤታን ተመረጡ፤ በከፍተኛ ድምፅ የሚደረደረውን በገና በመምታት የእነርሱ ረዳቶች እንዲሆኑም ዘካርያስ፥ ያዕዚኤል፥ ሸሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤሊአብ፥ ማዕሤያና በናያ ተመረጡ። በዝቅተኛ ድምፅ የሚደረደረውን በገና እንዲመቱ ማቲትያ፥ ኤሊፈሌ፥ ሚቅኔያ፥ ዐዛዝያ እንዲሁም ከቤተ መቅደስ ዘበኞች መካከል ዖቤድኤዶምና ዩዒኤል ተብለው የሚጠሩት ሰዎች ተመረጡ።