Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 40:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤ ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤ ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን፣ ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አበሠርሁ፥ እነሆ፥ ከንፈሮቼን አላግድም፥ አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አንተ ግን አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ አስ​ነ​ሣኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 40:10
25 交叉引用  

ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል።


የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትእዛዞች ለሚጠብቁ ሰዎች የእግዚአብሔር መንገዶች ሁሉ ፍቅርና ታማኝነት ናቸው።


ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።


እኔ ግን ስለ ያዕቆብ አምላክ ከመናገር ስለ ክብሩም ከመዘመር ከቶ አልቈጠብም።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ዘወትር እዘምራለሁ፤ እውነተኛነትህንም ለትውልድ ሁሉ እገልጣለሁ።


እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።


ዐመፀኛ ሕዝብ ስለ ሆኑ ቢሰሙህም ባይሰሙህም እኔ የምልህን ቃል ትነግራቸዋለህ።


ለቀደሙ አባቶቻችን በማልክላቸው መሠረት ለአብርሃምና ለያዕቆብ ዘር ታማኝነትህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያለህ።


ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ!’ ”


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያጸድቅበትን መንገድ ባለማወቃቸው የራሳቸውን የጽድቅ መንገድ ተከተሉ እንጂ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አልተከተሉም።


ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።


የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቆ ነበር፤ በዚህ ምክንያት እኛ ስለዚህ ጉዳይ ምንም መናገር አያስፈልገንም።


“ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ሁሉ የባስሁ ኃጢአተኛ እኔ ነኝ።


መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።


跟着我们:

广告


广告