37 ደጉን ሰው ተመልከት፤ ቅን የሆነውንም ሰው እይ፤ ሰላም ወዳድ ሰው ዘር ይወጣለታል።
37 ንጹሓንን ልብ በል፤ ቅኑንም አስተውል፤ የሰላም ሰው ተስፋ አለውና።
37 ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፥ ለሰላም ሰው ተተኪ ይወጣለታልና።
ዑፅ ተብላ በምትጠራ አገር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ከክፉ ነገር ሁሉ ርቆ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ምንም ነውር የሌለበት፥ ቅን ሰው ነበር።
ችግር ሲመጣ ክፉዎች ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በታማኝነታቸው ይጠበቃሉ።
የጽድቅ ሥራ ሰላምን ያስገኛል፤ ውጤቱም ዘለዓለማዊ የሕይወቱ ዋስትና ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ በቶሎ ከዚህ ዓለም በሞት እንደምለይ ዐውቃለሁ።