Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 35:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ይኸዋ የልባችን ምኞት ደረሰ!” ብለው እንዲያስቡና ወይም “እኛ አሸነፍነው!” እንዲሉ አታድርግ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በልባቸው፣ “ዕሠይ! ያሰብነው ተሳካ! ዋጥ አደረግነውም” አይበሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በልባቸው፦ እሰይ እሰይ፥ ነፍሳችንን ደስ አላት አይበሉ፥ ደግሞም፦ ዋጥነው አይበሉ።

参见章节 复制




መዝሙር 35:25
16 交叉引用  

የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”


የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።


በታላቅ ቊጣ በእኛ ላይ ተነሥተው ከነሕይወታችን በዋጡን ነበር፤


ለክፉዎች የሚፈልጉትን ነገር አትስጣቸው፤ ዕቅዳቸው እንዲሰምር አታድርግ።


የሐሰት ምስክሮች ዐመፅን እየተናገሩ በእኔ ላይ ስለ ተነሡ ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።


የክፋትን ሥራ ከሚሠሩ ክፉ ሰዎች ጋር አትውሰደኝ፤ እነርሱ ከጐረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይነጋገራሉ፤ በልባቸው ግን ተንኰል አለ።


እግዚአብሔር ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገልጣል።


እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


እነርሱም “ኑ በሥልጣናችን ሥር እናድርጋቸው” አሉ። በሀገሪቱ ያሉትን የተቀደሱ ቦታዎችን ሁሉ አቃጠሉ።


‘ጠላትማ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ሀብታቸውንም እካፈላለሁ፤ የፈለግኹትንም እወስዳለሁ፤ ሰይፌንም መዝዤ አጠፋቸዋለሁ’ ብሎ ነበር፤


ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።”


እርሱ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሎአል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው!”


በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ የሕግ መምህራን በልባቸው እንዲህ አሉ፤


ወዲያውኑ ኢየሱስ ይህን የልባቸውን ሐሳብ በመንፈሱ ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ስለምን በልባችሁ ይህን ታስባላችሁ?


ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይህም የሚሞተው የማይሞተውን በሚለብስበት ጊዜ “ሞት በድል ተዋጠ!” ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል።


跟着我们:

广告


广告