Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 34:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤ ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤ ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አፋ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አላ​ቀቁ፤ እሰይ፥ እሰይ፥ በዐ​ይ​ና​ችን አየ​ነው ይላሉ።

参见章节 复制




መዝሙር 34:21
22 交叉引用  

ንጉሥ አክዓብ በዚህ ዐይነት ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፤


አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።


እነርሱ ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እኛ ግን እንነሣለን፤ ጸንተንም እንቆማለን።


በእኔ ውድቀት “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ በኀፍረት ይሸማቀቁ።


ጠላቶቹን አደቅለታለሁ፤ የሚጠሉትንም ሁሉ ከፊቱ አጠፋለታለሁ።


እርሱ ስለ ክፋታቸው ይቀጣቸዋል፤ ስለ ኃጢአታቸውም ይደመስሳቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ያጠፋቸዋል።


ምግቡ በሙሉ በዚያው በተዘጋጀበት ቤት ውስጥ መበላት ስላለበት ወደ ውጪ አይውጣ፤ ከጠቦቱም አጥንቶቹን አትስበሩ።


“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።


ጻድቅ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ እንደ ገና ይነሣል፤ ዐመፀኞች ግን ጥፋት ይደርስባቸዋል።


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለ ነበር፥ ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም ሲሉ እርሱ ከሄደ በኋላ መልእክተኛ ላኩ።


በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው።


ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት እኔን ይጠላኛል።


እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ በመሆኑ መከራን በሚያመጡባችሁ ላይ መከራን በማምጣት ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።


እነርሱ ከጌታ ፊትና ከኀያል ክብሩ ተለይተው በዘለዓለም ጥፋት ይቀጣሉ።


ጋሻጃግሬው የነበረውንም ወጣት “እነዚህ ያልተገረዙ እኔን ወግተው በመሳለቅ መጫወቻ እንዳያደርጉኝ አንተ ራስህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ፈርቶ አልገደለውም፤ ስለዚህም ሳኦል ራሱ የገዛ ሰይፉን ወስዶ በስለቱ ላይ ወደቀበት።


跟着我们:

广告


广告