Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 31:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሕይወቴ በመጨነቅ፣ ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ ከመከራዬ የተነሣ ጕልበት ከዳኝ፤ ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ተቸግሬአለሁና አቤቱ ምራኝ፥ ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ደከመ፥ ነፍሴም ሆዴም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የኃ​ጥ​ኣን መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው ብዙ ነው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን ግን ይቅ​ርታ ይከ​ባ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制




መዝሙር 31:10
12 交叉引用  

በምግብ ፈንታ እቃትታለሁ፤ ጩኸቴም እንደ ፈሳሽ ውሃ ነው።


ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል? እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል? እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?


እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ጮክ ብዬ ስጣራ ስማኝ! ምሕረትን አድርግልኝ፤ ጸሎቴንም ስማ!


ከቊጣህ የተነሣ ሥጋዬ ደኅንነት የለውም። በኃጢአቴም ምክንያት መላ ሰውነቴ ጤንነት የለውም።


ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም፤ የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፤ በእርግጥ ሰው ከነፋስ ሽውታ የሚሻል አይደለም።


እግዚአብሔር የለቅሶዬን ጩኸት ሰምቶአል፤ ስለዚህ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ!


አሁንም በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ደካማ በምሆንበትም ጊዜ አትተወኝ።


ስለዚህ ዕድሜአቸውን እንደ እስትንፋስ አሳጠረ፤ ሕይወታቸውም በሽብር እንዲያልቅ አደረገ።


ከልጅነቴ ጀምሮ ጭንቀት ደርሶብኝ እስከ ሞት ተቃርቤአለሁ፤ ከማስደንገጥህ የተነሣ ተስፋ ቈርጬአለሁ።


ትልቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቤ አለ፤


跟着我们:

广告


广告