Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 21:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሡ የሚተማመነው በእግዚአብሔር ነው፤ የማያቋርጠው የልዑል እግዚአብሔር ፍቅር ከእርሱ ጋር ስለ ሆነም አይናወጥም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኗልና፤ ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ ከቆመበት አይናወጥም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስ ታሰኘዋለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የሚ​ያ​ዩኝ ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፤ ራሳ​ቸ​ውን እየ​ነ​ቀ​ነቁ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላሉ፦

参见章节 复制




መዝሙር 21:7
17 交叉引用  

እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤ በማዳንህ እደሰታለሁ።


ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! በቅንነትና ባለማወላወል በአንተ ተማምኜ ስለ ኖርኩ ፍረድልኝ።


በክብርና በግርማ የተሞላህ ኀያል ንጉሥ ሆይ፥ ሰይፍህን ታጠቅ።


በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በቤትህ እንድኖርና በጥበቃህ ሥር መጠለያ እንዳገኝ ፍቀድልኝ።


የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።


በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ለስምህ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።


እግዚአብሔርን “አንተ መከታዬና መጠጊያዬ ነህ፤ አንተ የምተማመንብህ አምላኬ ነህ” ይለዋል።


በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


እርሱ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሎአል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው!”


እንዲሁም “እምነቴን በእርሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል፤ እንደገናም “እነሆኝ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች እዚህ ነን” ይላል።


ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤


跟着我们:

广告


广告