Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 119:98 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

98 ትእዛዝህ መቼም ከአእምሮዬ ስለማይጠፋ፥ ከጠላቶቼ ሁሉ ይልቅ እኔን አስተዋይ ያደርገኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

98 ትእዛዞችህ ምን ጊዜም ስለማይለዩኝ፣ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረጉኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

98 ለዘለዓለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 119:98
12 交叉引用  

አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ።


ታማኝ ለመሆንና ሕግህን ለመጠበቅ ወስኜአለሁ።


ጥበብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም የሚገኙት ከእርሱ ዘንድ ነው።


ክፉ ሰዎች ፍትሕ ምን እንደ ሆነ አያውቁም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሰዎች ግን በሙሉ ያስተውሉታል።


እነርሱን በጥንቃቄ ጠብቁአቸው፤ ይህንንም ስታደርጉ በሌሎች ሕዝቦች ዘንድ ምን ያኽል ብልሆችና አስተዋዮች መሆናችሁን ታሳያላችሁ። እነዚህም ሌሎች ሰዎች ስለ ደንቦቹ ሲሰሙ ይህ ትልቅ ሕዝብ በእውነት ብልኅና አስተዋይ ነው ይላሉ።


የቱንስ ያኽል ታላቅ ቢሆን ዛሬ እኔ በፊታችሁ ቆሜ እንደማስተምራችሁ እንደዚህ ያለ ትክክልና ቅን የሆነ ሕግና ሥርዓት ያለው ሕዝብ የት ይገኛል?


የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።


ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ መርምሮ በእርሱ የሚጸና፥ እርሱንም ሰምቶ መርሳት ሳይሆን፥ በሥራ ላይ የሚያውለው ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል።


እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር።


የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች በየጊዜው እየመጡ ጦርነት ያደርጉ ነበር፤ ይሁን እንጂ በማናቸውም ጦርነት ሁሉ ከሳኦል የጦር መኰንኖች ይበልጥ ድል የሚሳካለት ለዳዊት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ዳዊት እጅግ ዝነኛ ሆነ።


ሳኦል በትእዛዝ በሚያዘምትበት ቦታ ሁሉ የዳዊት ተልእኮ የተሳካ ሆነ፤ ስለዚህም ሳኦል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የመኰንንነት ማዕርግ እንዲኖረው አደረገ፤ ይህም የሳኦልን የጦር መኰንኖችና ወታደሮችን ሁሉ አስደሰተ።


跟着我们:

广告


广告