147 ጎህ ከመቅደዱ በፊት ርዳታህን በመፈለግ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በገባህልኝም ቃል ተስፋ አደርጋለሁ።
147 ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድድ ተነሥቼ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ።
147 ማለዳ ጮኽሁ፥ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።
በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ፤ እኔም በማለዳ እነሣለሁ።
ተስፋ የማደርገው የአንተን ፍርድ ስለ ሆነ ዘወትር እውነት እንድናገር እርዳኝ።
በተስፋ ቃልህ ስለምታመን አንተን የሚያከብሩ ሁሉ እኔን በሚያዩበት ጊዜ ደስ ይበላቸው።
የአንተን አዳኝነት በሙሉ ልቤ እመኛለሁ። እምነቴን በቃልህ ላይ አድርጌአለሁ።
በብዙ በረከትን ሰጥተህ ተቀበልከው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ ደፋህለት።
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩን በቀን ይሰጣል፤ በሌሊትም የምስጋና መዝሙር አቀርብለታለሁ፤ ወደ ሕይወቴ አምላክ እጸልያለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ወደ አንተ አቅርቤ መልስህን ስጠብቅ በየማለዳው ጸሎቴን ስማ።
በእግዚአብሔር ስለምታመን አልፈራም፤ ስለ ሰጠኝም ተስፋ አመሰግነዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ስለምታመን ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
ነፍሴ ሆይ! ተነሺ፤ በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ! እኔም በማለዳ እነሣለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በየማለዳውም ወደ አንተ እጸልያለሁ።
እባክህ ጸሎቴን ስማ! ጩኸቴንም አድምጥ!
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
ሊነጋ ሲል፥ ኢየሱስ በማለዳ ተነሥቶ ወጣና ለመጸለይ ወደ አንድ ገለልተኛ ቦታ ሄደ፤