127 ትእዛዞችህን ከወርቅ ይልቅ አብልጬ እወዳለሁ፤ አዎ፥ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ አብልጬ እወዳለሁ።
127 ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ ትእዛዞችህን ወደድሁ።
127 ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቁ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።
የአንተን ትእዛዝ መፈጸም ብዙ ሀብት የማግኘትን ያኽል ያስደስተኛል።
በትእዛዞችህ የምደሰተው እነርሱን ስለምወዳቸው ነው።
ከብዙ ወርቅና ከብዙ ብር ይልቅ ለእኔ እጅግ ዋጋ ያለው አንተ የምትሰጠው ሕግ ነው።
እነርሱ ከንጹሕ ወርቅ የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው፤ ከማር ወለላ ይበልጥ ጣፋጮች ናቸው።
ወርቅን ከማግኘት ጥበብን ማግኘት ይበልጣል፤ ብርንም ከማግኘት ዕውቀትን ማግኘት ይሻላል።
“እኔ ጥበብ፥ ከዕንቊ የምበልጥ ስለ ሆንኩ ምንም ነገር ብትመኙ ከእኔ የሚወዳደር አንድም ነገር የለም።
እኔ ከቅዱሳን ሁሉ የማንስ ብሆንም እንኳ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ እንዳበሥር በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ዕድል ተሰጠኝ።