Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 109:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ሁሉ ክፉ ነገር በእኔ ላይ የሚናገሩትን ጠላቶቼን በዚህ ዐይነት ቅጣቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይህ ቅጣት በሚከሱኝና በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ላይ ከጌታ ዘንድ ይሁን።

参见章节 复制




መዝሙር 109:20
19 交叉引用  

አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።


ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ።


በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በደንብ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣሃል፤


እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።


ቊጣው በቅጽበት ስለሚነድ በእናንተ ላይ ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ በመንቀጥቀጥ ስገዱለት እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።


ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይመክራሉ፤ ሊገድሉኝ የሚፈልጉትም በእኔ ላይ ያሤራሉ።


እርሱ ስለ ክፋታቸው ይቀጣቸዋል፤ ስለ ኃጢአታቸውም ይደመስሳቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ያጠፋቸዋል።


የሰው ልጅ ደግሞ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፥ ‘እነሆ! ይህ መብልና መጠጥ የሚወድ ነው! የቀራጮችና የኃጢአተኞችም ወዳጅ ነው!’ አሉት። ሆኖም የጥበብ ትክክለኛነት ግን በሥራዋ ይረጋገጣል።”


ፈሪሳውያን ግን ይህን በሰሙ ጊዜ “እርሱ ‘ብዔልዜቡል’ በተባለው በአጋንንት አለቃ አማካይነት ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም” አሉ።


ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “በስሜ ተአምር እያደረገ ወዲያውኑ በእኔ ላይ ክፉ የሚናገር ስለሌለ ተዉት፤ አትከልክሉት፤


በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው።


ስለዚህ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ኢየሱስን የሚረግም ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው!” የሚል ማንም እንደሌለ እነግራችኋለሁ።


የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


跟着我们:

广告


广告