12 የሚራራለት ሰው ከቶ አይኑር፤ ድኻ ዐደግ ልጆቹን የሚንከባከባቸው ሰው አይገኝ።
12 ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
12 በቸርነት የሚያግዘውንም አያግኝ፥ ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
ልጆቹም የኑሮ ዋስትና አያገኙም፤ በአደባባይም የሚከራከርላቸው ስለማያገኙ ጥቃት ይደርስባቸዋል።
በቀስታቸውና በፍላጻቸው ወጣቶችን ይገድላሉ፤ ሕፃናትን እንኳ አይምሩም፤ ለልጆችም ርኅራኄ የላቸውም።
የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ወጣቶቻቸውን ይቀጣል፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶችና አሳዳጊ ለሌላቸው ለሙት ልጆቻቸው አይራራም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ከሐዲና ክፉ አድራጊ ሆኖአል፤ ከእያንዳንዱም ሰው አንደበት የሚነገረው ቃል ተንኰል የሞላበት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እነርሱን ለመቅጣት እጁ እንደ ተቃጣ ነው።
ሕዝቡም ሁሉ “በእርሱ ሞት ምክንያት የሚመጣው ቅጣት በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።
ስጡ፤ ለእናንተም ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ እንዲሁ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም በጥሩ መስፈሪያ ታምቆና ተጠቅጥቆ እስኪትረፈረፍ ድረስ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል።”
የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።