33 እጅግ አስመርረውት ስለ ነበር ሙሴ ራሱን ባለመቈጣጠር ተናገረ።
33 የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።
33 ወንዞችን ምድረ በዳ አደረገ፥ የውኃውንም ምንጮች ደረቅ አደረጋቸው፤
ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
ኢዮብም “እንዴት የሞኝ ሴት ንግግር ትናገሪያለሽ? እግዚአብሔር መልካም ነገር ሲሰጠን በደስታ እንቀበላለን፤ ታዲያ፥ መከራ ሲያመጣብን በእርሱ ላይ ማጒረምረም ይገባናልን?” አላት። ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ መከራና ሥቃይ ቢደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር በመናገር ኃጢአት አልሠራም።
“ይህ፥ ያለ ዕውቀት በሚነገሩ ቃላት ምክሬን የሚያቃልል እርሱ ማነው?
ይህም ሁሉ የደረሰባቸው በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ በማመፃቸውና ምክሩንም በመናቃቸው ነበር።
እግዚአብሔር ሆይ! ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።
እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤ በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።
በበረሓ ሳሉ ብዙ ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፁ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ አሳዘኑት።
እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።