Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 102:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ፤ ትውልዳቸውም በአንተ ዘንድ ጸንቶ ይኖራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

参见章节 复制




መዝሙር 102:28
14 交叉引用  

የአንተ ቀኖች እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን ወይስ ያንተ ዕድሜ እንደ ሰው ዕድሜ አጭር ነውን?


የሰጠኸውም የተስፋ ቃል “ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው።


ይህ እንዲሆን የፈቀደ ማን ነው? የታሪክንስ ሂደት የሚቈጣጠር ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ ነበርኩ፤ በመጨረሻም የምገኝ እኔው ነኝ።


እኔ ከጥንት ጀምሮ አምላክ ነኝ፤ ከእጄ ማንም ማንንም አያድንም፤ እኔ ያደረግኹትን መለወጥ የሚችል የለም።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይሁን እንጂ በሕማም አደቀው ዘንድ የእኔ ፈቃድ ነበር፤ ሕይወቱን የበደል መሥዋዕት አድርጎ በሚያቀርብበት ጊዜ ዘመኑ ተራዝሞ ብዙ ትውልድ ያያል፤ በእርሱም አማካይነት የእኔ ፈቃድ ይፈጸማል።


እነርሱ የሠሩትን ቤት ሌሎች አይገቡበትም፤ የተከሉትንም ማንኛውንም ነገር ባዕዳን አይበሉትም፤ ሕዝቤ እንደ ዛፍ ለረጅም ዘመናት ይኖራሉ፤ የመረጥኳቸውም ሰዎች የደከሙበትን ነገር ለረጅም ጊዜ ይደሰቱበታል።


“የምፈጥራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በእኔ ጸንተው እንደሚኖሩ እንዲሁም ዘራችሁና ስማችሁ በእኔ ጸንተው ይኖራሉ፤


“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ ስለዚህ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ገና ፈጽማችሁ አልጠፋችሁም።


“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም


跟着我们:

广告


广告