Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ ክፉ ሰዎች በፍርድ ቀን ከፍርድ አይድኑም፤ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ አይገኙም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ፊት፣ ኀጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር መቆም አይችሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚህ ዝን​ጉ​ዎች በፍ​ርድ፥ ኃጥ​ኣ​ንም በጻ​ድ​ቃን ምክር አይ​ቆ​ሙም።

参见章节 复制




መዝሙር 1:5
12 交叉引用  

ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤ በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል።


ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤ ሕይወቴንም አታጥፋ።


ትዕቢተኞች በፊትህ አይቆሙም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ትጠላለህ።


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


በዚያን ጊዜ በጻድቅና በኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር በሚታዘዝና በማይታዘዝ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት እንደገና ታያላችሁ።”


በዓለም መጨረሻም እንዲህ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን ይለዩአቸዋል።


ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ እርሱም ሕዝቦችን እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል።


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


ስለዚህ እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት ሲሄዱ፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።”


እነዚያን እግዚአብሔርን የማያመልኩትን ሰዎች ባደረጉአቸው ክፉ ነገሮች ምክንያት ይቀጣቸዋል፤ እግዚአብሔርም በእውነቱ በእነዚህ እርሱን በማያመልኩ ኃጢአተኞች ላይ በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ይፈርድባቸዋል።”


跟着我们:

广告


广告