Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እናንተ ዕውቀት የሌላችሁ፥ ዕውቀትን ለመገብየት ተማሩ፤ እናንተ ሞኞች፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እናንተ አላዋቂዎች፤ ጠንቃቃነትን ገንዘብ አድርጉ፤ እናንተ ሞኞች፤ ማስተዋልን አትርፉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥ እናንተም ሞኞች አስተውሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እናንተ የዋሆች፥ ጥበብን አስተውሉ፤ እናንተም ሰነፎች፥ ዕውቀትን ገንዘብ አድርጉ፤

参见章节 复制




ምሳሌ 8:5
15 交叉引用  

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።


ከሕዝብ መካከል እናንተ አላዋቂዎች ይህን አስተውሉ፤ እናንተ ሞኞች ሆይ! አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው?


“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!


ዕውቀት የጐደላቸው ሰዎች ከጥበብ በመራቃቸው ምክንያት ይሞታሉ፤ ሞኞችም ከቸልተኛነታቸው የተነሣ ይጠፋሉ።


በዕውቀት ላልበሰሉ ብልኅነትን ለወጣቶችም ዕውቀትንና ማስተዋልን እንዲያገኙ ያደርጋሉ።


ጠቢባን መልካም ክብርን ያገኛሉ፤ ሞኞች ግን ውርደትን ይከናነባሉ።


እኔ ጥበብ፥ ማስተዋል አለኝ፤ ዕውቀትና ትክክለኛ አስተያየት የእኔ ናቸው።


“ሰዎች ሆይ! እናንተን ሁሉ እጠራለሁ፤ ወደ ሰው ዘር ሁሉ እጣራለሁ፤


“ዕውቀት የጐደላችሁ ሰዎች ሁሉ ወደዚህ ኑ!” እያሉ እንዲጣሩ አደረገች፤ ሞኙንም ሰው እንዲህ ትለዋለች።


እግዚአብሔር እንደ ጀግና ወታደር ይወጣል፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጦርነትን ያውጃል፤ በጠላቶቹም ላይ ድልን ይጐናጸፋል።


ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’


እግዚአብሔር በዓለም ሰዎች ዘንድ አሉ ተብለው የሚታዩትን ነገሮች እንደሌሉ ለማድረግ በዓለም የተዋረደና የተናቀ ከንቱም መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ።


跟着我们:

广告


广告