Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ልጆቼ ሆይ! የአባታችሁን ምክር ስሙ፤ በጥንቃቄ አዳምጡ፤ ማስተዋልንም ታገኛላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤

参见章节 复制




ምሳሌ 4:1
15 交叉引用  

እናንተ የያዕቆብ ልጆች፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ።


ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።


ምሳሌዎቹም ጥበብንና መልካም ምክርን ለመገንዘብ፥ ጥልቅ አስተሳሰብ ያለውን የዕውቀት ቃል ለመረዳት የሚጠቅሙ ናቸው።


ልጄ ሆይ! የአባትህን ምክር ስማ፤ እናትህ የምታስተምርህንም ሁሉ አትናቅ።


ብልኅ ልጅ የአባቱን ምክር ይቀበላል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።


ምክርን ብትሰማና ለመማርም ፈቃደኛ ብትሆን የኋላ ኋላ ጥበብ መገብየትህ አይቀርም።


ጠቢባን ሰዎች የተናገሩትን ሳስተምርህ አድምጥ፤ ከእነርሱ የምታገኘውን ትምህርት አጥና፤


ልጄ ሆይ! እኔ ወደምነግርህ ጥበብና ማስተዋል አተኲረህ አድምጥ።


ጥበብን እንደ እኅትህ፥ ማስተዋልንም እንደ ቅርብ ወዳጅህ አድርገህ ቊጠራቸው።


ኢዮናዳብ የሰጠንን ትምህርት ሁሉ ተቀብለናል፤ እኛም ሆንን ሚስቶቻችን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም የወይን ጠጅ አንጠጣም፤


ስለዚህ ከሰማነው ነገር ተንሸራትተን እንዳንወድቅ ስለ ሰማነው ነገር በጣም መጠንቀቅ አለብን።


跟着我们:

广告


广告