6 “በሞት ጣር ላይ ለሚገኙና በሥቃይ ኑሮ ወይንና የሚያሰክር መጠጥ ስጡአቸው።
6 ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣ በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤
6 ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፥ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት፥
ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርስዋ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።
ለሞት የተቃረቡትን ሰዎች ስለምረዳ መረቁኝ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ስለምረዳቸው በደስታ ይዘምሩ ነበር።
“በጭንቀት ላይ ላሉ ብርሃን፥ ኑሮአቸው በመራራ ሐዘን ለተመላ ሕይወት የሚሰጣቸው ለምንድነው?
ስለዚህ ልቡን ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፥ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና ብርታት የሚሰጠውን ምግብ ያዘጋጃል።
እነርሱ ድኽነታቸውንና ሥቃያቸውን እንዲረሱ ይጠጡ።
ይህን ሁሉ ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ ስለ ሆነ፥ ምን ማለት እችላለሁ? ከምሬቴ የተነሣ እንቅልፌ ሁሉ ጠፍቶ ነበር።
ስለ ሆድህ ሕመምና ስለ ዘወትር ደዌህ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ውሃ ብቻ አትጠጣ።
እርስዋም ከልብዋ ሐዘን የተነሣ ምርር ብላ እያለቀሰች ወደ እግዚአብሔር ጸለየች።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤