22 ስስታም ሀብታም ለመሆን ሲጣደፍ ድኽነት በቶሎ የሚመጣበት መሆኑን አይገነዘብም።
22 ስስታም ሀብት ለማከማቸት ይስገበገባል፤ ድኽነት እንደሚጠብቀውም አያውቅም።
22 ምቀኛ ሰው ሀብታም ለመሆን ይጣደፋል ችጋርም እንደሚመጣበት አያውቅም።
ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።
በጥንቃቄ በወጣ ዕቅድ የሚሠራ ሥራ ትርፍ ያስገኛል፤ ያለ ዕቅድ በችኰላ የሚሠራ ሥራ ግን ያደኸያል።
ለሀብታሞች ስጦታ የሚሰጥ፥ ወይም ሀብት ለማግኘት ብሎ ድኾችን የሚጨቊን ሰው ይደኸያል።
የስስታምን እንጀራ አትብላ፤ የሚያቀርብልህም ጥሩ ምግብ አያስጐምጅህ፤
ታማኝ ሰው የተባረከ ሕይወት ይኖረዋል፤ ሀብታም ለመሆን የሚስገበገብ ሰው ግን ቅጣት ያገኘዋል።
በገዛ ገንዘቤ የፈለግኹትን ማድረግ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ ለጋሥ ስለ ሆንኩ አንተ ትመቀኛለህ?’ ”
አመንዝራነት፥ ስግብግብነት፥ ክፋት፥ አታላይነት፥ ስድነት፥ ምቀኝነት፥ ሐሜተኛነት፥ ትዕቢት፥ ግዴለሽነት ናቸው።
ሀብታሞች ለመሆን የሚፈልጉ ግን በፈተና ይወድቃሉ፤ ሰዎችን በሚያበላሽና በሚያጠፋ ከንቱና አደገኛ በሆነ በብዙ ምኞት ወጥመድ ይያዛሉ።