Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 28:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አንድ ሰው የሰውን ሕይወት ቢያጠፋ እስኪሞት ድረስ እየሸሸ ይኑር፤ ማንም ሰው አያስጠጋው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የሰው ደም ያለበት ሰው፣ ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ ማንም ሰው አይርዳው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የሰው ደም ያለበት ሰው እስከጉድጓድ ይሸሻል፥ ማንም አያስጠጋውም።

参见章节 复制




ምሳሌ 28:17
16 交叉引用  

ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ምንም ፍሬ አትሰጥህም፤ በምድር ላይም ስደተኛ ሆነህ ትንከራተታለህ።”


ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።


በዚህም ጊዜ አቤሴሎም ሸሽቶ አምልጦ ነበር፤ ለዘብ ጥበቃ ተረኛ የነበረውም ወታደር ልክ በዚያን ሰዓት ከሖርናይም ወደዚህ በሚመጣው መንገድ ላይ ካለው ኮረብታ ብዙ ሕዝብ ወደ ታች ሲወርድ አየ፤ ወደ ንጉሡም ቀርቦ ያየውን ሁሉ ተናገረ፤


ከዚያም በኋላ የኢዮአብ አጃቢዎች ከሆኑ ወታደሮች ዐሥሩ ወደ አቤሴሎም ሄደው ዙሪያውን በመክበብ በጦር መሣሪያ ገደሉት።


ኢዮአብ ወደ ተቀደሰ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ።


እኔ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የምለው ይህ ነው ‘ናቡቴን መግደልህ አንሶህ ሀብቱንም ልትወርስበት ነውን?’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ እንዲሁም የአንተን ደም ይልሱታል!’ ”


ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ ሬሳዋን በኢይዝራኤል ከተማ ውስጥ ውሾች ይበሉታል፤


‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።


ይሁን እንጂ ሰው በቊጣ ተነሣሥቶና ሆን ብሎ ሌላ ሰው ቢገድል፥ ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ።


በንቀት የሚመለከት ዐይን፥ ሐሰትን የሚናገር ምላስ፥ ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፥


እስማኤልና ስምንት ሰዎቹ ግን ከዮሐናን እጅ አምልጠው ወደ ዐሞን ምድር ኰበለሉ።


የማልታ ሰዎች እባብ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው! ከባሕሩ ማዕበል በደኅና ቢወጣም ከአምላክ ፍርድ አምልጦ በሕይወት ለመኖር አልቻለም” ተባባሉ።


“ነገር ግን አንድ ሰው በጠላትነት ተነሣሥቶ በመሸመቅ ሆን ብሎ በጭካኔ ሌላውን ሰው ከገደለ በኋላ ሕይወቱን ለማትረፍ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፤


跟着我们:

广告


广告