Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 28:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሀብታም ሰው ዘወትር ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፤ አስተዋይ የሆነ ድኻ ግን የእርሱን ጠባይ መርምሮ ያውቃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ባለጠጋ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥር ይሆናል፤ አስተዋይ የሆነ ድኻ ግን መርምሮ ያውቀዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሀብታም ሰው ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል፥ አስተዋይ ድሀ ግን ይመረምረዋል።

参见章节 复制




ምሳሌ 28:11
18 交叉引用  

ሰዎችን ጠቢባን የሚያደርጋቸው ሽምግልና አይደለም፤ ትክክለኛውንም ነገር ለማስተዋል የሚረዳቸው የዕድሜ ብዛት አይደለም።


ሀብታሞች ግን ሀብታቸው በከተማ ዙሪያ እንዳለ ከፍተኛና ጠንካራ ግንብ የሚጠብቃቸው ይመስላቸዋል።


በአደባባይ በመጀመሪያ ቀርቦ የሚናገር ሰው ተከራካሪው መጥቶ ጥያቄ እስከሚያቀርብለት ድረስ፥ ዘወትር እርሱ ብቻ ትክክል የሆነ ይመስለዋል።


በንግግሩ ከሚቀላምድ ሞኝ ሰው ይልቅ በቅንነት የሚኖር ድኻ ሰው ይሻላል።


ለመበልጸግ አትድከም፤ ከዚህ ዐይነት ስግብግብነት ለመራቅ ጥበበኛ ሁን፤


በራሱ አስተሳሰብ ጠቢብ የሆነ ከሚመስለው ሰው ይልቅ ሞኝ ሰው ተስፋ አለው።


ሰነፍ፥ በቂ ማስረጃ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይበልጥ አስተዋይ የሆነ ይመስለዋል።


ሆኖም ጠቢብ ነኝ ብሎ እንዳይመጣ ሞኝነቱን በመግለጥ መልስለት።


“እኔ ዐዋቂ ነኝ” አትበል። ይልቅስ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ከክፋትም ራቅ።


ራሳቸውን ብልኆችና ጥበበኞች አድርገው ለሚቈጥሩ ወዮላቸው!


ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው።


እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።


የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።


跟着我们:

广告


广告