Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 27:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጊዜ የሚያመጣውን ነገር ስለማታውቅ ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነገ በሚሆነው አትመካ፤ ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ቀኑ ምን እንደሚያመጣ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።

参见章节 复制




ምሳሌ 27:1
9 交叉引用  

ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “ ‘እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም’ ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።


ሃማን ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ከዚህም ሁሉ በላይ ንግሥት አስቴር ባዘጋጀችው ግብዣ ላይ ከንጉሡና ከእኔ በቀር ማንንም አልጠራችም፤ ለነገ በምታዘጋጀው ግብዣም ላይ እንደገና ተጠርተናል፤


እርሱ አምላካችን ነው፤ እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤ ስለዚህ ዛሬ እንዲህ ሲል የሚናገረውን አድምጡ፦


ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለይቶ የሚያውቅ ሰው የለም፤ “ይህ ይሆናል” ብሎ የሚነግረውስ ማነው?


እነርሱም፦ ‘ኑ ወይን ጠጅ እንፈልግ በጠንካራ መጠጥም እንርካ! ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል!’ ይላሉ!”


እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”


ስለዚህ እርሱ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ ነገ አንተና ልጆችህ እኔ ወዳለሁበት ቦታ ትመጣላችሁ፤ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”


跟着我们:

广告


广告