28 ዋሾ አንደበት የሚጐዳቸውን ሰዎች ይጠላል፤ የሽንገላ ንግግርም ጥፋትን ያመጣል።
28 ሐሰተኛ ምላስ የጐዳቻቸውን ትጠላለች፤ ሸንጋይ አንደበትም ጥፋትን ታመጣለች።
28 ሐሰተኛ ምላስ ያቈሰላቸውን ሰዎች ይጠላል፥ ልዝብ አፍም ጥፋትን ያመጣል።
በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፥ “አንተ ወደዚህ ያመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር።
እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ።
ወዳጆቹን የሚያቈላምጥ ሰው ለእግራቸው ወጥመድ ይዘረጋል።
ከመጥፎ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ይረዱሃል።
እነርሱ ከአመንዝራ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ያደርጉሃል።
እኔ ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።