23 የሰሜን ነፋስ ዝናብን እንደሚያመጣ ሐሜትም ቊጣን ማስከተሉ የተረጋገጠ ነው።
23 የሰሜን ነፋስ ዝናብ እንደሚያመጣ ሁሉ፣ ሐሜተኛ ምላስም ቍጡ ፊት ታስከትላለች።
23 የሰሜን ነፋስ ዝናብ ያመጣል፥ ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቈጣል።
ከሰሜን በኩል ወርቅ የመሰለ ብርሃን ይመጣል፤ እግዚአብሔርም በሚያስደንቅ ግርማ ይገለጣል።
ብርቱ ነፋስ ከደቡብ ይነሣል። ብርዳማ ነፋስም ከሰሜን ይመጣል።
ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም።
ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥ በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥
ክፉዎች ሰዎች እንደሚያደርጉት እነርሱ በክፋት አፌዙብኝ፤ በእኔም ላይ ጥርሳቸውን አፋጩ።
እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ አሾክሿኪ ከሌለም ጠብ ይቆማል።
የሰውን ስም የሚያጠፉ፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ሰውን የሚያዋርዱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን ለማድረግ ዘዴ የሚፈልጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
እኔ ወደዚያ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት ልትሆኑ እንደምፈልገው ሳትሆኑ፥ እኔም እናንተ እንደምትፈልጉት ሳልሆን እንገናኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ፤ እንዲሁም በእናንተ ዘንድ ጥል፥ ቅናት፥ ቊጣ፥ ራስ ወዳድነት፥ የሰው ስም ማጥፋት፥ ሐሜት፥ ትዕቢትና ሁከት ይኖሩ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ።