Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 22:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ምንም ስለሌላቸው፥ ድኾችን አትበዝብዝ፤ የተጨቈኑትንም ሰዎች በፍርድ ሸንጎ አታጒላላ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ድሀን አትግፈፈው ድሀ ነውና፥ ችግረኛውንም በበር አትጨቁነው፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ድሃን በግድ አትበለው፥ ድሃ ነውና ችግረኛውንም በበር አትግፋው፤

参见章节 复制




ምሳሌ 22:22
15 交叉引用  

“ድኾች የሚለምኑትን ከልክዬ አላውቅም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች ከማጽናናት አልተቈጠብኩም።


በፍርድ ሸንጎ ተሰሚነት ያለኝ መሆኔን በማወቄ በሙት ልጅ ላይ እጄን አንሥቼ አላውቅም።


ድኻ ለፍርድ ቢቀርብ ድኽነቱን በማየት አድልዎ አታድርግለት።


“በፍርድ አደባባይ አድልዎ በማድረግ የድኻውን ፍርድ አታጣምበት፤


ዐመፀኞች መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ስለማይወዱ በግፍ ሥራቸው ይጠፋሉ።


ለሀብታሞች ስጦታ የሚሰጥ፥ ወይም ሀብት ለማግኘት ብሎ ድኾችን የሚጨቊን ሰው ይደኸያል።


የድኾች መብት እንዳይከበርና የተበደሉ ፍትሕ እንዳያገኙ የምታደርጉበት ዘዴ ይኸው ነው፤ በዚሁ ዘዴ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና አሳዳጊ የሌላቸውን የሙት ልጆች ንብረት ትነጥቃላችሁ።


የሀገሪቱ ሰዎች ዝርፊያና ቅሚያ ያካሄዳሉ፤ ድኾችን፥ ችግረኞችንና መጻተኞችን ፍትሕ በመንሣት ይበድላሉ።


“በጐረቤትህ ላይ ግፍ አትሥራ፤ ወይም ንብረቱን አትቀማው፤ ቀጥረህ የምታሠራውን ሰው ደመወዝ ለአንድ ሌሊት እንኳ በአንተ ዘንድ አይደር።


አንዱ እስራኤላዊ በሌላው እስራኤላዊ ላይ ግፍ አይሥራ፤ አምላካችሁን ፍሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


በመካከላችሁ የሚኖሩትን ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ አባትና እናት የሌላቸውን ድኻ አደጎች፥ መጻተኞችንና ችግረኞችን አትጨቊኑ፤ እርስ በርሳችሁ አንዳችሁ ሌላውን ለመጒዳት አታስቡ።’


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


ከከተሞችህ በአንዱ በመረጠው ስፍራ ከአንተ ጋር በመካከልህ ይኑር እንጂ አታስጨንቀው።


跟着我们:

广告


广告