Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 22:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጠቢባን ሰዎች የተናገሩትን ሳስተምርህ አድምጥ፤ ከእነርሱ የምታገኘውን ትምህርት አጥና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የጠቢባንን ቃል ልብ ብለህ ስማ፤ ልብህም ወደ ትምህርቴ ያዘንብል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፥ ልብህንም ወደ እውቀቴ አድርግ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ።

参见章节 复制




ምሳሌ 22:17
16 交叉引用  

ሕዝቤ ሆይ! ትምህርቴን አድምጥ፤ ቃሌንም በጥንቃቄ ስማ፤


ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል ዕድሜአችን ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስተምረን።


እነርሱም እውነትን ፍትሕንና ቅንነትን በመከተል ሥርዓትንና ጥበብን ወደ ተሞላ ሕይወት ይመራሉ።


አእምሮህን በትምህርት ላይ፥ ጆሮህንም ዕውቀትን በመስማት ላይ አውላቸው።


የጥበበኞች ተጨማሪ አባባሎች፦ በዳኝነት ማዳላት ስሕተት ነው፤


ልጄ ሆይ! የማስተምርህን አትርሳ፤ ትእዛዞቼንም በልብህ ጠብቅ።


የጠቢባን ንግግር፥ እረኛ የከብቶቹን መንጋ እንደሚነዳበት ጫፉ እንደ ሾለ በትር ነው፤ በአንድነት የተከማቹ ምሳሌዎች ጠልቀው እንደሚገቡ ምስማሮች ናቸው፤ እነርሱም ከሁላችን ጠባቂ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው።


ጥበብንና የነገሮችን ሁናቴ ለመረዳት፥ ለማጥናትና ለመመርመር አሰብኩ፤ ይህም ክፋት ሞኝነት መሆኑን፥ ሞኝነትም እብደት መሆኑን ወደማወቅ አደረሰኝ።


ጥበበኛ ለመሆንና በዚህ ዓለም የሚደረገውንም ነገር ሁሉ መርምሬ ለማወቅ በሞከርኩ መጠን ሰው ሌት ከቀን ዕረፍት አጥቶ እንደሚኖር ተረዳሁ።


በዚህ ዓለም የሚካሄደውን ሁናቴ በጥሞና ስመለከት ይህን ሁሉ አስተዋልኩ፤ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለመጒዳት ሥልጣን የሚኖረው ለምንድን ነው?


“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።


ጴጥሮስ ገና ይህን ሲናገር ሳለ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።


跟着我们:

广告


广告