Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 21:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በመዋሸት የሚገኝ ሀብት ተኖ እንደሚጠፋ እንፋሎትና እንደሚገድል ወጥመድ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፥ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን የሚያከማች ከንቱ ነገርን ይከተላል፥ ወደ ሞት ወጥመድም ያደርሰዋል።

参见章节 复制




ምሳሌ 21:6
12 交叉引用  

አግባብ ባልሆነ መንገድ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ቀጥተኛነት ግን ከሞት ያድናል።


ያለ ድካም በቀላሉ የተገኘ ሀብት ወዲያው ይጠፋል፤ ተግቶ በመሥራት የተገኘ ሀብት ግን እየበዛ ይሄዳል።


ገዢ ዘወትር መጥፎ ነው እያለ ዕቃን ያራክሳል፤ ገዝቶ ከሄደ በኋላ ግን “በርካሽ ገዛሁ” እያለ ይመካል።


በመጀመሪያ ያለ ድካም በቀላሉ የሚገኝ ሀብት በመጨረሻ አይባረክም።


ኃጢአትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤ ቊጣውም የትም አያደርሰውም።


ሰውን ከማታለልና ሐሰት ከመናገር ጠብቀኝ፤ የሚያስፈልገኝን ያኽል ምግብ ስጠኝ እንጂ ሀብታም ወይም ድኻ አታድርገኝ።


እኔን ያጣ ራሱን ይጐዳል፤ እኔን የሚጠላም ሞትን ይወዳል።”


ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሀብትን የሚሰበስብ፥ ያልጣለችውን ዕንቊላል ታቅፋ እንደምትፈለፍል ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ የሰበሰበውን ሃብት ሁሉ ያጣል። በመጨረሻም ሞኝነቱ ግልጥ ይሆናል።


ከክፉ ሥራችሁ ሁሉ ተላቃችሁ አዲስ መንፈስና አዲስ ልብ ይኑራችሁ፤ እናንተ እስራኤላውያን ለምን ትሞታላችሁ?


እነዚህን ሰዎች ዝም ማሰኘት ይገባል፤ እነርሱ በሚያሳፍር ትርፍ ለማግኘት የማይገባውን ነገር እያስተማሩ ቤተሰቦችን በሙሉ ያናውጣሉ።


እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!


跟着我们:

广告


广告