Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 20:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔር የምንራመድበትን መንገድ ወስኖአል፤ ታዲያ፥ ሰው ሕይወቱ ወዴት አቅጣጫ እንደሚያመራ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የሰው አካሄዱ ከጌታ ዘንድ ነው፥ እንግዲስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቃናል፤ ሟች ግን መንገዱን እንዴት ያውቃል?

参见章节 复制




ምሳሌ 20:24
10 交叉引用  

እግዚአብሔርን የሚፈሩ እነማን ናቸው? እነርሱ መከተል የሚገባቸውን አካሄድ እንዲመርጡ እርሱ ያስተምራቸዋል።


አምላክ ሆይ! ዱካህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ።


እግዚአብሔር በሰው አካሄድ ከተደሰተ የእርምጃውን ትክክለኛነት ያረጋግጥለታል።


የብልኅ ሰው ጥበብ መንገዱን እንዳይስት ያደርገዋል። ሞኝን ሰው ግን ሞኝነቱ መንገዱን እንዲስት ያደርገዋል።


ሰው ዕቅድ ያወጣል፥ ነገር ግን ዕቅዱ በሥራ ላይ የሚውለው እግዚአብሔር ይሁን ብሎ ሲፈቅድ ብቻ ነው።


ሰው ዕቅድ ያወጣል፤ ነገር ግን ዕቅዱ ከግቡ የሚደርሰው በእግዚአብሔር ርዳታ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! ሰው በራሱ ሕይወት እንደማያዝበትና አካሄዱንም በራሱ ሥልጣን መቈጣጠር እንደማይችል ዐውቃለሁ።


ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ከቤተ መቅደሱ ተዘርፈው የመጡትን የወርቅ ዕቃዎች አስመጥተህ አንተና መኳንንቶችህ፥ ሚስቶችህና ቁባቶችህ የወይን ጠጅ መጠጫ አደረጋችኋቸው፤ ከጠጣችሁም በኋላ ማየት ወይም መስማት የማይችሉትንና ምንም ነገር የማያውቁትን ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገናችሁ፤ መግደል ወይም ማዳን የሚችለውንና አካሄድህን የሚቈጣጠረውን ሕያው አምላክ ግን አላከበርከውም።


‘ሕይወት የምናገኘውና የምንንቀሳቀሰው፥ የምንኖረውም በእርሱ ነው፤’ ይህም የእናንተ ባለ ቅኔዎች ‘እኛ ሁላችን የእርሱ ልጆች ነን’ እንዳሉት ነው።


跟着我们:

广告


广告